Skip to main content

Find food near you

በ SNAP Double Up Food Bucks በኦሪገን ያደጉ ተጨማሪ ትኩስ ምርቶችን በማግኘት ይደሰቱ (AMH)

Fresh produce that you can get for free with Oregon Food Stamps.

ትኩስ፣ በአገር ውስጥ የሚበቅሉ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን በእጥፍ ወደ ቤት ማምጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ - ይህም ለቤተሰብዎ ያለ ምንም ተጨማሪ ወጪ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?

የእርስዎን የ Oregon Trail EBT ( "SNAP" ወይም "Food Stamps" በመባል የሚታወቀው) ካርድ ተሳታፊ በሆኑ የገበሬዎች ገበያ እና የግሮሰሪ ሱቆች ላይ፣ በ SNAP Double Up Food Bucks ፕሮግራሞች ላይ በሚጠቀሙበት ጊዜ የምታወጡትን እያንዳንዱ ዶላር እጥፍ እንዲሆን ያደርጋል። ፕሮግራሙ በኦሪገን ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ቦታዎች ላይ ይሰራል፤ ይህም የተለያዩ የታወቁ ባህላዊ፣ እና ባህላዊ ምግቦችን የሚያቀርቡ የራሳቸው ባለቤትነት ያላቸው ሱቆች ያጠቃልላል። በአመታዊ የእርሻ ድርሻ (CSA) አባልነትዎ ላይ ትልቅ ቅናሽ ለማግኘት Double Up መጠቀም ይችላሉ!

ይህ የመረጃ ምንጭ፡ ለኦሪገን ነዋሪዎችን በሚሰጠው SNAP Double Up Food Bucks ጥቅማጥቅሞች ላይ ያተኮረ ነው። በነዚህ ዋሽንግተን ወይም Idaho አካባቢዎች ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማግኘት የእርስዎን Oregon SNAP EBT ጥቅማ ጥቅሞችን መጠቀም ይችላሉ።

እዚህ ላይ እንጀምር

Volunteer: Sign UpA raised fist holding a pencil. Illustration.

Double Up Food Bucks እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ስለ SNAP የምታውቁ ከሆነ እና ስለ Double Up የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ እዚህ ላይ የበለጠ መረጃ መግኘት ይችላሉ፡-

እንዴት እንደሚሰራ

Find Support: Network

Double Up Food Bucks የት መጠቀም እችላለሁ?

Double Up ን የሚቀበሉ የአከባቢ ሱቆችን እና የገበሬ ገበያዎችን ለማግኘት እየፈላለጉ ከሆነ፡ ይህ ካርታ ሊረዳዎት ይችላል፡-

በአቅራቢያ ያሉ ቦታዎችን ይፈልጉ

Find Support: Free Food

የ SNAP ጥቅሞች ለማግኘት ብቁ ነኝ?

ለጥቅማጥቅሞች ለመቀበል ብቁ መሆንዎን ወይም አለመሆንዎን እርግጠኛ ካልሆኑ፡ ብቁ መሆንዎን ለማወቅ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ጠቃሚ መሳሪያ ይኸው፦

ብቁነትን ያረጋግጡ

ስለ SNAP Double Up Food Bucks ወይም ፕሮግራሙ ቤተሰብዎን እንዴት እንደሚረዳ በተመለከተ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት፡ እዚህ ላይ ማንበብ ይቀጥሉ!

እንዴት እንደሚሰራ

Oregon SNAP can get you more fresh produce.

በገበሬ ገበያዎች የሚገኙ Double Up Food Bucks

ፍራፍሬ፣ አትክልት ወይም የአትክልት ጅምር/ዘሮች ለመግዛት የሚጠቅም እስከ $20 ያህል ዶላር-ለዶላር መልስ ለማግኘት የ Double Up ቶከኖችን ወይም ኩፖኖችን ይጠቀሙ።

ተጨማሪ ለማወቅ

Get double the produce at farmers markets, grocery stores and CSAs with Oregon EBT

በግሮሰሪ ሱቆች ውስጥ ያሉ Double Up Food Bucks

በዚያ ቦታ ላይ Double Up ን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለማወቅ ተሳታፊ በሆኑ የግሮሰሪ ሱቆች ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ ይጠይቁ። በግሮሰሪ ሱቆች፡ የእርስዎን የ Double Up ጥቅሞችን በኩፖን፣ በሱቅ ካርድ ወይም በአውቶማቲክ ቅናሽ በኩል ሊያገኙት ይችላሉ።

ተጨማሪ ለማወቅ

Get more shallots and onions with your food stamps in Oregon.

Double Up Food Bucks በእርስዎ የእርሻ ድርሻ/ CSA

አጭር ቅጽ ከሞሉ በኋላ፣ የእርስዎ የ Double Up Food Bucks የ Oregon Trail Card’s SNAP ምግብ ጥቅማጥቅሞችን በመጠቀም በሚገዙት ምርቶች ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ።

ተጨማሪ ለማወቅ

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

SNAP Double Up Food Bucks ሲባል በትክክል ምንድን ነው?

ከ Fair Food Network ብሔራዊ ሞዴል የተወሰደ፣ የ Oregon Double Up Food Bucks ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኦረገን ነዋሪዎች ቤተሰብ የሆኑ ገበሬዎችን እና የአካባቢ ኢኮኖሚዎችን እየደገፉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በብዛት መመገብ ቀላል ያደርገዋል። Double Up የኦረገን የመጀመሪያ ግዛት አቀፍ የማበረታቻ ፕሮግራም ሲሆን፡ ለገዢዎች ምቹ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ፕሮግራሙ ተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ፕሮግራም (አንዳንድ ጊዜ "SNAP" ወይም "food stamps" ተብሎ የሚጠራው) በተሳታፊ ገበሬዎች ገበያዎች፣ የግሮሰሪ ሱቆች እና በ CSA (በማህበረሰብ የተደገፈ ግብርና) እርሻዎችን ጥቅማጥቅሞች በእጥፍ ያሳድጋል ስለዚህ ሸማቾች ብዙ ትኩስ ምርቶችን ወደ ቤት ማምጣት ይችላሉ። በአሁኑ ጊዜ Double Up ከ85 በላይ የገበሬዎች የገበያ ቦታዎች፣ 35 የግሮሰሪ ሱቆች እና ከ40 በላይ የ CSA እርሻዎች በመላ ግዛቱ ይቀርባል - እንዲሁም ፕሮግራሙን በየዓመቱ የሚቀላቀሉ አዳዲስ ቦታዎች አሉ።

Double Up ከ SNAP ጋር እንዴት ይዛመዳል?

የተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ፕሮግራም (SNAP) ገቢ ዝቅተኛ ሲሆን ምግብ ለመግዛት የሚረዳ በመንግስት የተደገፈ ፕሮግራም ነው። ጥቅማጥቅሞች የ SNAP EBT ካርድ ተብሎ በሚጠራው ላይ ትጫናል፣ አንዳንዶች ደግሞ “Oregon Trail Card” ብለው ይጠሩታል። ካርዱ ልክ እንደ ዴቢት ካርድ የሚያገለግል ሲሆን፡ ነገር ግን ገንዘቡ የምግብ ምርቶችን ለመግዛት ብቻ ይውላል።

የእያንዳንዱ ሰው የ EBT ካርድ በግል ገቢያቸው እና በቤተሰባቸው ሁኔታ ላይ በመመስረት የተለያየ የገንዘብ መጠን አለው - አንድ ብቻ የቤተሰብ አባል ያለው ሰው በወር እስከ $234 ወይም አራት የቤተሰብ አባል ያላቸው ሰዎች እስከ $782 ገንዘብ ይኖረዋል። ማመልከቻዎ በሚጸድቅበት ጊዜ ዝርዝሮችን ያገኛሉ። በየወሩ የ SNAP ፕሮግራም ጥቅምን ያገኛሉ፤ ይህንን የጥቅም መጠን በካርድዎ ውስጥ ይጨመራል እና ምግብ ለመግዛት ሊያገለግል ይችላል። ጥቅም ላይ ያልዋሉ ገንዘቦች ወደ ካርድዎ ከተጨመሩበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ አመት ድረስ ይቆያሉ።

በተጨማሪም፣ ብዙ ሱቆች እና የገበሬዎች ገበያዎች የ SNAP ተቀባዮች የሚያገልግል በ Double Up Food Bucks ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ፤ ይህም በአገር ውስጥ ከሚበቅሉ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ሲገዙ በየቀኑ እስከ $20 ድረስ የሚያስገኝ ፕሮግራም ነው። የ SNAP ካርድ ተጠቃሚዎች ትኩስ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለመግዛት በተሳታፊ ሱቆች፣ የገበሬዎች ገበያዎች እና የምግብ ትብብር ሱቆች ሲገዙ ለሚያወጡት ለእያንዳንዱ $1 ዶላር Double Up $1 ተመላሽ ክፍያ ያገኛሉ። በዚፕ ኮድ ሊፈለግ የሚችል የተሳታፊ ሱቆችን የሚያሳይ ካርታ ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

የ SNAP Double Up Food Bucks ጥቅማ ጥቅሞችን ለምን መጠቀም እችላለሁ?

በግሮሰሪ ሱቆች Double Up የሚከተሉትን ለመግዛት ሊያገለግል ይችላል፡-

  • ትኩስ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች

  • ትኩስ ቅጠሎች

  • እንጉዳዮች

  • የአትክልት፣ የቅጠሎች ወይም የፍራፍሬ ትክል ቡቅያ

  • የአትክልት፣ የቅጠሎች ወይም የፍራፍሬ ተክሎች ዘሮች

በገበሬዎች ገበያዎች Double Up ለሚከተሉት መጠቀም ይቻላል፡-

  • ትኩስ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች

  • ትኩስ ቅጠሎች

  • የቀዘቀዙ እና የደረቁ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች

  • እንጉዳዮች

  • ባቄላ

  • የአትክልት፣ የቅጠሎች ወይም የፍራፍሬ ተክል ቡቅያ

  • የአትክልት፣ የቅጠሎች ወይም የፍራፍሬ ተክል ቡቅያ

Double Up ለሚከተሉት መጠቀም አይቻልም፦

  • ጨው፣ ስኳር፣ ስብ፣ ወይም ዘይት የተጨመረበት ማንኛውም የፍራፍሬ ወይም የአትክልት ምርት

  • ለምሳሌ የታሸጉ ፍራፍሬዎች ወይም አትክልቶች፣ በከረጢት የታሸጉ ሰላጣዎች ከቅመሞች ጋር፣ በመያዣ የሚሸጡ ፍራፍሬዎች ወይም ስኳር የተጨመረበት ጭማቂ

SNAP Double Up ከሚሰጠው በላይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የእኛ FoodFinder መጠቀም መጀመሩ ጥሩ ነው! ነጻ የምግብ ገበያዎች፣ ጓዳዎች እና የምግብ ጣቢያዎች ለማግኘት የሚሰራ የ Oregon Food Bank Network SNAP የማይሸፍናቸው አንዳንድ ምንጮችን ማግኘትዎን ያረጋግጣል።
የ SNAP Double Up Food Bucks ጥቅሞችን ለመቀበል ብቁ የሆነው ማነው?

Double Up Food Bucks ካርድዎ ከየትም ይሁን ከየት ለሁሉም የ SNAP ተጠቃሚዎች የሚገኝ ይሆናል። ለምሳሌ፣ የዋሽንግተን SNAP ካርድ ያላቸው ደንበኞች የ Double Up ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት በኦሪገን ላይ የተመሰረተ የግሮሰሪ ሱቅ ወይም የገበሬ ገበያ ላይ ማመልከት ይችላሉ። Double Up Food Bucks በተመለከተ እዚህ ላይ ተጨማሪ ያግኙ

የሚቀበሉት ዋናው የ SNAP ገንዘብ መጠን በእርስዎ ገቢ እና በቤተሰብዎ ውስጥ ባሉ ሰዎች ብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ልብ ይበሉ - የምግብ ግዢዎን በሚጋሩት ሰዎች። ነገር ግን ሁሉም ሰው በሚገዙበት ቦታ ላይ በመመስረት ከፍተኛው የ Double Up ተመላሽ ክፍያ ለማግኘት ብቁ ነው። ስለ SNAP የብቁነት መመሪያዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የመረጃ ገጻችንን ይመልከቱ።

Double Up Food Bucks እንዴት ነው የሚደገፈው እና የሚካሄደው?

Double Up Food Bucks አገልግሎት መስጠት የሚችለው በ Oregon Food Bank፣ Farmers Market Fund፣ Pacific Northwest CSA Coalition፣ እና Oregon Farmers Markets Association መካከል ባለው የአጋርነት ድጋፍ ነው። አንድ ላይ በመሆን ከ85 በላይ የገበሬዎች የገበያ ቦታዎች፣ 35 የግሮሰሪ ሱቆች እና ከ40 በላይ እርሻዎች ላይ Double Up ን እንደግፋለን።

የእኛ ግላዊ፣ መሰረታዊ እና የማህበረሰብ ስፖንሰሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ አባላት ከአካባቢው አርሶ አደሮች እና ምግብ አምራቾች የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ በመላው ግዛት ድርጅት እንድናድግ አስችሎናል። Double Up በ Gus Schumacher Nutrition Incentive Grant Program ቁጥር 2020-70030-33183 / 1024374 እና 2022-70415-38570/1029309 ከ USDA ብሔራዊ የምግብ እና ግብርና ተቋም - እንዲሁም ከ Gus Schumacher Nutrition Incentive Program Covid Relief & Response Grant Program ቁጥር 2021-70034-35369 / 1027071 ይጋፍ ያገኛል።

በግሮሰሪ ሱቆች ውስጥ Double Up ን እንዴት እጠቀማለሁ?

በመላው ግዛቱ ተሳታፊ የሆኑ ግሮሰሪዎች ላይ ብቁ እቃዎችን ሲገዙ Double Up ዶላር መጠቀም ይችላሉ። የ SNAP EBT ካርድዎን ተሳታፊ ወደሆነው የግሮሰሪ ሱቅ ይዘው ይምጡ እና የሚወዷቸውን ትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ይግዙ። በ SNAP ውስጥ ለሚያወጡት እያንዳንዱ $1፣ እስከ $20 የሚደርስ ለተጨማሪ ትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ለመግዛት የሚያስችል $1 የ Double Up Food Bucks ያገኛሉ። በግሮሰሪ ሱቆች ላይ የእርስዎን Double Up በኩፖን፣ በሱቅ ካርድ ወይም በአውቶማቲክ ቅናሽ በኩል ሊያገኙ ይችላሉ። በዚያ ቦታ ላይ በትክክል እንዴት Double Up ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ ተሳታፊ በሆነው ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ገንዘብ ተቀባይ ወይም ሰራተኛ ይጠይቁ። በግሮሰሪ ሱቆች ውስጥ Double Up ን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚገልጹ ተጨማሪ ዝርዝሮች በ Double Up Food Bucks ድህረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Double Up በገበሬዎች ገበያዎች እንዴት ይሰራል?

በመላው ግዛቱ በሚገኙ የገበሬዎች ገበያዎች ላይ ብቁ እቃዎችን ሲገዙ Double Up ዶላር መጠቀም ይችላሉ። መግዛት ከመጀመርዎ በፊት የ SNAP EBT ካርድዎን ከእርስዎ ጋር ይዘው ተሳታፊ ወደሆነው የገበሬዎች ገበያ ይዘው ይምጡ እና የመረጃ ቋቱን ይጎብኙ። በ SNAP ውስጥ ለሚያወጡት እያንዳንዱ $1፣ እስከ $20 የሚደርስ ለተጨማሪ ትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ለመግዛት የሚያስችል $1 የ Double Up Food Bucks ያገኛሉ። ለምሳሌ፡ የ SNAP ጥቅምን በመጠቀም $20 ከከፈሉ፡ ተጨማሪ ምርት ለመግዛት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ነጻ $20 ተጨማሪ ያገኛሉ።

በአብዛኛዎቹ የገበሬ ገበያዎች Double Up ቶከኖች/ኩፖኖች እያንዳንዳቸው $2 ዋጋ አላቸው፣ ስለዚህ የአንድ ዶላር አሃዝ በ SNAP ጥቅማጥቅሞች መግዛቱ ሙሉውን የተመላሽ ክፍያ ማግኘት እንደሚችሉ ያረጋግጣል። ለምሳሌ፡ የ $5 ዋጋ SNAP ተጠቅመው ከገዙ፡ በ Double Up $4 ብቻ ያገኛሉ፤ ነገር ግን በ SNAP ውስጥ $6 ከጠየቁ ሙሉውን $6 በ Double Up ያገኛሉ።

አጠቃላይ በየቀኑ የሚሰጥ የ Double Up ተመላሽ ክፍያ የገበሬዎች የገበያ ቦታን መሰረት በማድረግ ይለያያል። የሚገዙበትን ዕለታዊ የተመላሽ ክፍያ መጠን ለማወቅ ተሳታፊ የሆኑትን የግሮሰሪ ሱቆችን፣ የገበሬ ገበያዎችን እና የ CSA ን ሙሉ ዝርዝር ይመልከቱ። በገበሬዎች ገበያ ውስጥ Double Up ን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚገልጹ ተጨማሪ ዝርዝሮች በ Double Up Food Bucks ድህረ ገጽ ላይ ይገኛሉ

የእኔ ማህበረሰብን የሚደገፍ የግብርና (CSA) ፕሮግራም በተመለከተ Double Up Food Bucks እንዴት አገኛለሁ?

የ CSA ፕሮግራሞች ለመጽሔት ከሚያደጉት ምዝገባ ጋር የሚመሳመሉ ሲሆን፡ ነገር ግን ለምግብ ነው የሚደረጉት! በየሳምንቱ የአከባቢዎ ገበሬ የተለያዩ ትኩስ፣ አልሚ ምግቦችን በአካባቢዎ ወዳለ ምቹ ቦታዎች ያቀርባል። የ CSA/ farmshare ከተሳታፊ እርሻ ለመግዛት የ SNAP የምግብ ጥቅማ ጥቅሞችን በ Oregon Trail Card ሲጠቀሙ፡ የ Double Up Food Bucks በክፍያዎ ላይ በቀጥታ ይጨመራሉ። ለመፈረም እና ለመላክ አጭር ቅጽ ሊኖር ይችላል፡ ነገር ግን አጠቃላይ ሂደቱ ቀላል ነው። የ Double Up ጥቅምን በ CSA እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚገልጹ ተጨማሪ ዝርዝሮች ከ Pacific Northwest CSA Association ይገኛሉ

የእርስዎ ልምድ እና የውክልና ድጋፍ አስፈላጊ ነው!

በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ሁሉ በረሃብ የተጋረጡ ሰዎችን ዋና ጉዳይ እናደርጋለን።

እንደ Double Up Food Bucks የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ሁላችንም ጤናማ ምግብ ማግኘታችንን ለማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን የአስርተ አመታት ልምድ እንደሚነግረን የምግብ እርዳታ መስጠት ብቻውን ረሃብን ለማቆም በቂ መፍትሔ አይደለም። ለዚህም ነው በማህበረሰባችን ውስጥ ረሃብን የሚያስከትሉ ፖሊሲዎችን እና ስርዓቶችን ለመለወጥ ጠንክረን የምንሰራው። ረሃብን ከስሩ ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ውስጥ እንዴት መሳተፍ እንደሚችሉ ለማወቅ የድርጊት ማንቂያዎችን እንዲያገኙ ይመዝገቡ


ከፌደራል የሲቪል መብቶች ሕግ እና የዩናይትድ ስቴትስ የእርሻ መምሪያ [U.S. Department of Agriculture (USDA)] የሲቪል መብቶች ደንቦች እና ፖሊሲዎች ጋር በተያያዘ፣ ይሄ ተቋም በዘር፣ በቆዳ ቀለም፣ በትውልድ አገር፣ በጾታ (በጾታ ማንነት እና በወሲብ አዝማሚያ ጨምሮ)፣ በሃይማኖት እምነት፣ በአካለስንኩልነት፣ በዕድሜ፣ በፖለቲካ እምነቶች መሰረት አድሎ እንዳያደርጉ፣ ወይም ከዚህ ቀደም ለተሳተፉበት የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ የተነሳ የበቀል ወይም የአፀፋ እርምጃ እንዳያከናዉኑ ይከለክላል።

የፕሮግራሙ መረጃዎች ከእንግሊዘኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሌሎች ቋንቋዎች እንዲሰጡ ይደረጋሉ። የፕሮግራሙን መረጃ ለማግኘት የተለየ የመግባቢያ ዘዴ የሚያስፈልጋቸው አካለ ስንኩላን ሰዎች (ለምሳሌ እንደ ብሬል፣ በትልቅ ፊደል ሕትመት፣ የድምጽ ቅጂዎች፣ የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ)፣ ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙበት ኤጀንሲ (ግዛት ወይም ኤጀንሲ) አግኝተው ማነጋገር አለባቸው። መስማት የተሳናቸው፣ መስማት ላይ የሚቸገሩ፣ ወይም የመናገር እክል ያለባቸው ሰዎች በፌደራል ሪሌ ሰርቪስ (Federal Relay Service) (800) 877-8339 በኩል USDA ን ደውለው ማነጋገር አለባቸው።

በፕሮግራሙ ላይ የተፈጠረ የአድሎ ሁኔታ ላይ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የ USDA ፕሮግራም የአድሎ አቤቱታ ማቅረቢያ ቅጽ የሆነው ቅጽ AD-3027 መሙላት አለባቸው፣ ቅጹ ኦንላይን በዚህ አገናኝ፦ https://www.fns.usda.gov/sites...፣ ወይም ከማንኛውም የ USDA ቢሮ፣ በ (833) 620-1071 ላይ በመደወል፣ ለ USDA የሚላክ ደብዳቤ በመፃፍ ይገኛል። ደብዳቤው የአቤቱታ አቅራቢውን ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ እና ተፈጽሟል የተባለውን የሲቪል መብቶች ጥሰት ሁኔታ እና ቀን፣ ጉዳዩን የሚመለከተውን የሲቪል መብቶች ምክትል ሴክረታሪ[Assistant Secretary for Civil Rights (ASCR)] መጥቀስ፣ ተፈጽሟል የተባለውን የአድሎ አሰራር በቂ በሆነ ሁኔታ በዝርዝር ማስፈር አለበት። የተሞላው የ AD-3027 ቅጽ ወይም ደብዳቤ በሚከተለው አድራሻ በኩል መቅረብ አለበት፦

1. በደብዳቤ፦
Food and Nutrition Service, USDA
1320 Braddock Place, Room 334
Alexandria, VA 22314; ወይም

2. ፋክስ፦
(833)-256-1665 ወይም (202)-690-7442; ወይም

3. ኢሜይል፦
FNSCIVILRIGHTSCOMPLAINTS@usda.gov
ይሄ ተቋም ሁሉንም ደንበኛ በእኩሌታ የሚመለከት ነው።

Related posts

News

Oregon Food Bank Concerned About the Impact of President Trump's Executive Orders on Our Community

News

Part three: Food justice means centering Indigenous leadership

News

Part two: Decolonizing food systems with Indigenous practices and First Foods

Email sign-up

Stay connected

Sign up to receive emails with updates, resources and ways to get involved.